መጽሐፈ ሲራክ 26
26
1መልካም ሚስት ያለው ባል እንደምን የተባረከ ነው፤ ዕድሜውም በእጥፍ ይረዝማል። 2ጥሩ ሚስት ለባልዋ ደስታ ናት፤ ሕይወቱም ሰላም የሰፈነባት ትሆናለች። 3መልካም ሚስት እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ከተተው ድርሻዎች፤ ከሁሉም የላቀችው ናት። 4ሃብታም ሆኑ ድሀ፥ ልቦቻቸው በደስታ ይሞላሉ፤ በማንኛውም ወቅት ፊቶቻቸው የብርሃን ጸዳል ይለብሳሉ። 5ሦስት የሚያስደነግጡኝ ነገሮች አሉ፤ አራተኛውም ያስፈራኛል፤ በመላው ከተማ የሚነገር ሐሜት፤ የሕዝብ ሁከተትና የሐሰት ክስ፥ ከሞት የከፋ አስደንጋጭ ድርጊቶች ናቸው። 6በሴት የምትቀና ሴት ግን የልብ ቁስል ናት፤ ይህም የምላስ መቅሰፍት ነው። 7ክፉ ሚስት በትክክል እንደማይገጥም ቀምበር ናት፤ እርሷን ለመግራት መሞከር ጊንጥ እንደ መያዝ ነው። 8ጠጪ ሚስት እጅግ ታስቆጣለች፥ ውርደቷን ልትደብቅም አትችልም። 9የሴት ዘማዊነት በድፍረቷ ይታወቃል፤ ቅንድቧም ይመሰክርባታል። 10ከደፋሯ ሴት ልጅህን በሚገባ ጠብቅ፤ ካልሆነ ግን ምንም ከማድረግ አትመለስም። 11ኀፍረት የማያውቁ ዐይኖቿን ተከታተል፤ ብታዋርድህ አይድነቅህ። 12ጥም እንዳቃጠለው መንገደኛ አፏን ትከፍታለች፤ የገኘችውንም ውሃ ትጠጣለች፤ በየድንኳኑ ፊት ለፊት ትቀመጣለች፤ ለመጣው ፍላጻም ሰገባዋን ትከፍታለች። 13የሚስት ሞገስ ባልዋን ያስደስታል፤ አያያዟም ኃይልን ይሰጠዋል። 14ረጋ ያለች ሚስት የእግዚአብሔር ስጦታ ናት፤ መልካም አስተዳደግ በዋጋ አይተመንም። 15ትሑት ሚስት እጥፍ ትርፍ ናት፤ ከንጹሕ ባሕርይ በላይ የሚወደድ የለም። 16በእግዚአብሔር ተራሮች ላይ እንደምታብራው ፀሐይ ሁሉ፥ በጥሩ ቤት ውስጥ ያለ የመልካም ሴት ውበት እንዲሁ ነው። 17በመልካም ቁመና ላይ የሚታይ ቁንጅና፥ በተቀደሰ መቅረዝ ላይ እንደሚያበራ ፋኖስ ነው። 18ቀጥ ባሉ ተረከዞች ላይ የተሰኩ ውብ ባቶች፥ በብር መሠረት ላይ እንደተተከሉ የወርቅ ምሰሶዎች ናቸው።#26፥18 19 ሌጄ ሆይ፥ የወጣትነትህን አፋላ ጉልበት ጠብቅ፥ ጉልበትህንም ለባዕዳን አታባክን። 20 በምድር ሁሉ ላይ ለም የሆነውን ስፍራ ፈልግ፥ የራስህን ዘር ካስቀመጥክበት አውጥተህ በመተማመን ዝራ። 21 ዘርህ እንዲሁ እንዲለመልም፥ እናም በታላቅነት፥ ከመልካም በመምጣታቸው ላይ እምነት እያሳደሩና እያደጉ ይቆማሉ። 22 የምትከራይ ሴት እንደ ምራቅ ትፋት ትቆጠራለች፤ ካገባች ሴት ጋር መማገጥ በሚገድል ወጥመድ ውስጥ መግባት ነው። 23 አምላክ የለሽ የሆነች ሚስት ለክፉው ሰው ድርሻው ናት፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን አምላኩን ለሚፈራ ሰው ትሰጣለች። 24 ሐፍረት የሌላት ሴት ነቀፋን ትከናነባለች፤ ጥሩ ሴት ልጅ ግን በባሏም ፊት ቁጥብ ናት። 25 ደፋር የሆነች ሴት እንደ ውሻ ናት፤ ይሉኝታን የምታውቅ ግን ፈሪሃ እግዚአብሔር አላት። 26 ባሏን የምታከብረው ሚስት በሁሉም ዘንድ ጠቢብ ናት፤ ነገር ግን በኵራት የሚገባውን ክብር ብትነፍገው፥ በሁሉም ዘንድ በአምላክ የለሽ ትታወቃለች። እድሜው ይረዝማልና መልካም ሚስት ያለችው ባል ደስ ይበለው። 27 ጩኸታምና ወሬኛ የሆነች ሚስት እንደ መለከት ነጋሪት ትቆጠራለች፤ በዚህ ሁኔታ የሚኖር ሰው ሕይወቱን ስርዓት አልበኛ በሆነ ጦርነት መሀል እንደሚያሳልፍ ነው።
አሳዛኝ ነገሮች
28ልቤን የማያሳዝኑት ሁለት ነገሮች አሉ፤ ሦስተኛው ደግሞ ያስቆጣኛል። በድኀነቱ የተነሣ ወድቆ የሚቀር ጀግና፥ በጥላቻ ዐይን የሚታይ ጠቢብ፥ ከደግነት ወደ ኃጢአት ፊቱን የመሰለ ሰው፥ እግዚአብሔር ለአሰቃቂ ሞት መርጦታል።
ንግድ
29ነጋዴ ከስሕተት፥ አትራፊ ከኃጢአት ይነጻል ለማለት እጅጉን ይከብዳል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 26: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ