መጽሐፈ ሲራክ 25
25
ምሳሌዎች
1ነፍሴ የምትደሰትባቸው ሦስት ነገሮች አሉ፤ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ዘንድ ደስታን ይፈጥራሉ። እነርሱም የወንድማማቾች ስምምነት፥ የጐረቤት መዋደድና፥ የሚግባቡ ባልና ሚስት ናቸው። 2ነፍሴ የምትጠላቸው ሦስት ዓይነት ሰዎች አሉ። ህልውናቸውም ያንገበግበኛል። እርሱም ትዕቢተኛ ድኃ፥ ውሸታም ሀብታምና፥ ሐፍረተ-ቢስ ዘማዊ ሽማግሌ ናቸው።
ሽማግሌዎች
3በወጣትነትህ ምንም ካልያዝህ በሽምግልና ዕድሜህ ምን ታገኛለህ? 4ከነጭ ጠጉር ትክክለኛ ፍርድ፥ ከሽበት ጺም መልካም ምክር ሲገኝ ምንኛ እንደምን ያስደስታል! 5ከሽማግሌዎች ጥበብ፥ ከታላላቅ ሰዎች ዘንድ ምክር ሲገኝ እንደምን ያስደስታል! 6የሽማግሌዎች አክሊል በሳል ተሞክሮ፥ ክብራቸውም እግዚአብሔርን መፍራት ነው።
አኃዛዊ ምሳሌዎች
7ደስተኞች ናቸው ብዬ የማስባቸው ዘጠኝ ሰዎች አሉ፤ አሥረኛው ምላሴ ላይ ነው፥ በልጆቹ የሚኮራ፥ የጠላቶቹን ውድቀት በዓይኑ የሚያይ፥ 8መልካም ሚስት ያለችው፥ ከበሬና ከአህያ ጋር የማይደክም፥ በምላሱ ክፉ ያልተናገረ፥ ከርሱ ላነሱ ሰው ያላደረ፥ የታደለ ነው። 9ብልህነትን ያገኘ፥ ለሚናገረው አድማጭ የማያጣ ደስተኛ ነው። 10ጥበብን የቀሰመ ታላቅ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ግን ከሁሉም የላቀ ነው። 11እግዚአብሔርን መፍራት ከሁሉም በላይ ነው፥ ይህን ጥበብ ከተካነው ሰው ጋር ሊስተካከል የሚችል ይኖራልን?#25፥11 12. እግዚአብሔርን መፍራት እርሱን የመውደድ መጀመሪያ ነው፤ ይሁንና አንድ ሰው ከእርሱ ጋር መተሳሰር የሚጀምረው በእምነት ነው።
ሴቶች
13ከማንኛውም ዓይነት ቁስል ይልቅ የልብ ቁስል የከፋ ነው። ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ይልቅ የሴት ክፋት አስፈሪ ነው። 14ጠላትህ ከሚያደርስብህ ሰቆቃ የከፋ ሰቆቃ አይኖርም። ከጠላትህ በቀል የከፋ በቀል አይኖርም። 15ከእባብ መርዝ የባሰ መርዝ የለም፤ ከጠላትህ ቁጣ የከፋ ቁጣ አይኖርም። 16ከክፉ ሴት ጋር ከመኖር፥ ከአንበሳ ወይም ከዘንዶ ጋር መኖርን እመርጣለሁ። 17የሴት ጥላቻ ፊትዋን ይለውጠዋል፤ እንደ ድብም ያከስለዋል። 18ባሏ ከጐረቤቶቹ ጋር ከእራት ሲወጣ፤ ሳይወድ በኀዘን ያቃስታል። 19የሴትን ጥላቻ የሚያህል ከቶ ምንም የለም፤ የኃጢአተኛው ዕጣ ይውደቅባት፤ 20ጨቅጫቃ ሚስት ያለው ጨዋ ወንድ፤ በአሸዋ ጉብታ ላይ እንደሚራመድ ሽማግሌ ነው። 21በሴት ልጅ ውበት አትማረክ፤ ስለ እርሷም ራስህን አትሳት። 22ባል በሚስቱ ላይ ጥገኛ በሆነበት ቤት፤ መጥፎ ባሕርይ፥ ውርደትና ኀፍረት ይነግሣሉ። 23ተስፋ መቁረጥ፤ የትካዜ መልክ፥ የልብ ስብራት፥ ይህ ሁሉ የክፉ ሚስት ውጤት ነው። የደከመ፥ እጅ የላመ ጉልበት፥ ባሏን ከምታሳዝን ሴት የሚገኝ በረከት ነው። 24ኃጢአት በሴት ተጀመረ፤ ዕድሜ ለእርሷ ሁላችን እንሞታለን። 25ለውሃ ቀዳዳ እንደማይተው፥ ለክፉ ሴትም ምላስ እንዲሁ ልጓም ያሻዋል። 26አንተ የምትላት ካልፈጸመች፥ ከቤትህ ትውጣ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 25: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ