መጽሐፈ ሲራክ 23
23
1አባቴና የሕይወቴ መሪ ጌታ ሆይ፥ ለእነርሱ ፈቃድ እንድገዛ አትተወኝ፤ ይጠሉኝም ዘንድ አትፍቀድ። 2ሐሳቤን የሚሸነቁጥልኝ፥ የጥበብንም ሕግ በልቤ የሚያስረጽ፥ ስሕተቶቼን ፈጽሞ የማያልፍ፥ ኃጢአቴንም የሚመረምር እርሱ ከቶ ማነው? 3ስህተቶቼ እንዳይበዙ፥ ኃጢአቴ እንዳይከመር፥ በጠላቶቼ ፊት እንዳልወድቅና ድሉም የእነርሱ ሆኖ እንዳይፈነጥዙ፥ 4አባቴ፥ የሕይወቴ አምላክ ጌታዬ ሆይ! ለዐይኖቼ ትዕቢትን አትስጥ። 5ምቀኝነትን ከእኔ ዘንድ አርቅ፥ 6ፍትወትና ለሥጋ ምኞት አታስገዛኝ፥ ወሰን ላጣ ፍላጐት አሳልፈህ አትስጠኝ።
መሐላ
7ልጆች ሆይ! ትምህርቴን አድምጡ፥ እርሱን የሚፈጽም ከቶውንም በወጥመድ አይገባም። 8ኃጢአተኛው በከናፍሩ ተጠምዷል፤ ተሳዳቢውና ትዕቢተኛውም በእነርሱ ተጠልፎ ይወድቃል። 9#ማቴ. 5፥34፤ ያዕ. 5፥12።መሐላ አይልመድብህ፥ የቅዱስ እግዚአብሔርን ስም በዋዛ አትጥራ። 10በቅርብ የሚቆጣጠሩት አገልጋይ ሰንበር እንደማያጣው ሁሉ፥ በእርሱ የሚምልና ስሙንም የሚጠራ ሰው ከቶውንም ከኃጢአት አይነጻም። 11ሁልጊዜ የሚምል ሰው በኃጢአት የተሞላ ነው፤ ምንጊዜም ከቤቱ መቅሠፍት አይጠፋም። እርሱ ከበደለ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ይወድቃል፤ ካለመጠንቀቅ የፈጸመው ከሆነ ደግሞ፤ ኃጢአቱ ድርብ ይሆንበታል። በሐሰት ከማለ ይቅርታ አይደረግለትም፤ ቤቱም በመቅሠፍት ይሞላል።
ጸያፍ ንግግር
12እንደ ሞት ያለ ንግግር አለ፤ ከቶ ይህን የመሰለ አነጋገር በያዕቆብ ዘር አይገኝ። 13ግርድፍና ጸያፍ ቋንቋን በአንደበትህ አታስለምድ፤ ኃጢአትን ያዘው ቃላት ናቸውና። 14በታላላቆች መሀል ስትቀመጥ አባትና እናትህን አስብ፤ በውስጣቸው መኖርክን ዘንግተህ፥ የሞኝ ባሕርይ እዳታሳይ ተጠንቀቅ፥ ይህን ብታደርግ አለመፈጠርህን ትመኛለህ፤ የተወለድክበትንም ቀን ትረግማለህ። 15ጸያፍ ቋንቋን የአፍ መፍቻው ያደረገ፥ በሕይወት እስካለ ድረስ ራሱን ከዚህ ስሕተት ሊያርቅ አይችልም።
አመንዝራነት
16ኃጢአትን በኃጢአት ላይ የሚፈጽሙ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፤ ሦስተኛው ደግሞ ቁጣን ያመጣል። 17እንደ ምድጃ ላይ እሳት የሚንቀለቀል ፍላጐት፤ እስካልረካ ድረስ አይጠፋም። ሥጋውን ለፍትወት የሚመኝ፥ እስኪቃጠል ድረስ ምኞቱ አይቆምም። ለሚልከሰከስ ምግብ ሁሉ ጣፋጭ ነው፤ እስኪሞት ድረስ ከዚያ አይርቅም። 18በትዳሩ ላይ የሚባልግ፥ ማን ያየኛል? በጨለማ ተከብቤያሁ፥ በግድግዳዎችም መሀል ተከልያለሁ፥ ማንም ስለማያየኝ ከቶ የሚያስጨንቀኝ ምንድነው? ልዑል እግዚአብሔር ኃጢአቴን አይዘክረውም ብሎ ያስባል። 19እሱ የሚፈራው የሰዎችን ዐይን ነው፤ የእግዚአብሐርን ዐይኖች ዐሥር ሺህ ጊዜ ከፀሐይ የበሩ መሆናቸውን ግን አይገነዘብም። የሰውን ባሕርይ እጅግ ሥውር መሸሸጊያዎችንም ሳይቀር ዘልቆ እንደሚያይ አልተከሠተለትም። 20ከመፈጠራቸው በፊት ለእርሱ ሁሉም ይታወቃሉ፤ ከተፈጠሩ በኋላ ዛሬም ያውቃቸዋል። 21ይህ ሰው በከተማው ሕዝብ ፊት ይቀጣል፥ ባልጠበቀበትም ጊዜ ይያዛል።
ዘማዊት
22ለባሏ የማትታመንና ወራሹን ከሌላ የምትወልድለት ሴትም፥ ቅዥትዋ እንዲሁ ይሆናል። 23በመጀመሪያ የልዑል እግዚአብሔርን ሕግ አፍርሳለች፥ ሁለተኛ በባሏ ላይ ወስልታለች፤ ሦስተኛ በዝሙት አድፋ 24ከሌላ ወንድ ፀንሳለች፤ በጉባኤ ፊት ትቀርባለች፤ ስለ ልጅችዋም ትጠይቃለች፤ 25ልጆችዋ ሥር አይኖራቸውም፥ ቅርንጫፎቿም ፊጽሞ አይጠፋም። 26የተረገመ ትውስት ትታ ታልፋለች፤ እፍረቷም ፈጽሞ አይጠፋም። 27ያዩዋትም ሁሉ እግዚአብሔርን ከመፍራት የበለጠ ነገር እንደሌለ ይገነዘባሉ፤ ትእዛዛትን መፈጸምም ከሁሉ የተሻለ መሆኑን ይረዳሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 23: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ