መጽሐፈ ሲራክ 2
2
በፈተና ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት
1ልጄ ሆይ ጌታን ማገልገል ስትፈልግ፤ እራስህን ለፈተና አዘጋጅ፤ 2ቅን ልብ ይኑርህ፥ ቆራጥ ሁን፥ በጭንቀት ጊዜ አትታወክ፥ 3ወደ እግዚአብሔር ተጠጋ፥ ከሱ አትራቅ፥ በመጨረሻ ቀኖችህም ክብርን ትጐናጸፋለህ። 4የሚመጣብህን ነገር ሁሉ ተቀበለው፤ በመከራ ጊዜ ግራ ብትጋባም ታገስ። 5#ጥበ. 3፥5፤6፤ 1ጴጥ. 1፥7።ወርቅ በእሳት እንደሚፈተነው ሁሉ፥ በእግዚአብሔር የተመረጡ ሰዎችም የሚፈተኑት በውርደት ምድጃ ነው። 6በእግዚአብሔር ታመን፥ ይረዳሃል፤ ትክክለኛውን መንገድ ተከተል፤ ተስፋህም በእርሱ ላይ ይሁን፤ 7እናንተ ጌታን የምትፈሩ ምሕረቱን ተጠባበቁ፤ እንዳትወድቁ ከሱ አትራቁ። 8እናንተ ጌታን የምትፈሩ በሱ ተማመኑ፤ የሚገባችሁ ዋጋ አይቀርባችሁም፤ 9እናንተ ጌታን የምትፈሩ፥ የእርሱን መልካም ስጦታዎች ደስታንና ምሕረትን ተስፋ አድርጉ። 10ያለፉትን ትውልዶች ተመልከቱ፥ እዩ፤ እስቲ ማነው በጌታ ተማምኖ ያፈረ? 11ማነው እግዚአብሔርን በመፍራት ጸንቶ የተጣለ? ማነው እግዚአብሔርን ለምኖ ያልተሰማ? ምክንያቱም እግዚአብሔር ርኁርኀና መሐሪ ነው፤ ኃጢአትን ይቅር የሚልና በጭንቀት ጊዜ የሚያድን ነው። 12ስንፍና ለሚያጠቃቸው ልቦችና፥ ብርታት ለሌላቸው እጆች ወዮላቸው፤ በሁለት መንገድ የሚሄድ ወላዋይ ኃጢአተኛ ወዮለት። 13ብርታትና እምነት የሌለው ልብ ወዮለት፤ ምክንያቱም ጠባቂ የለውም። 14እናንተ ጸንታችሁ ያልኖራችሁ ወዮላችሁ፤ ጌታ ሲጐበኛችሁ ምን ልታደርጉ ነው? 15#ጥበ. 6፥18፤ ዮሐ. 14፥15፤21፤23።ጌታን የሚፈሩ ሰዎች፤ ከቶ ቃሉን አይጥሱም፤ እግዚአብሔርን የሚወዱ መንገዶችን ይጠብቃሉ፤ 16ጌታን የሚፈሩ ሁሉ፥ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ይፈጽማሉ፤ እሱን የሚወዱ በሕጉ ይረካሉ። 17ጌታን የሚፈሩ ሁልጊዜ ዝግጁ ልብ አላቸው፤ በፊቱ ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፤ እንዲህም ይላሉ፥
18በሰው እጅ ከምንወድቅ በእርሱ እጅ እንውደቅ፤
ምሕረቱ እንደ ታላቅነቱ ነውና።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 2: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ