መጽሐፈ ሲራክ 19
19
1ጠጪ ሠራተኛ አይበለጽግም፤ ትናንሾቹን ጉዳዮች የሚያቀል ቀስ በቀስ ይሰምጣል። 2ወይን ጠጅና ሴቶች ዓዋቂዎችን ከስሕተት ይጥላሉ፤ ሴተኛ አዳሪዎችን የሚያዘወትር፥ ብሎ ብሎ አፍረተ ቢስ ይሆናል። 3አፍረተ ቢሱ ውርስነቱ ለትሎች ነው፤ ሕይወቱንም ያጣል።
ከልቅ ንግግር ስለመታቀብ
4ለማመን የሚቀድም ማስተዋል ይጐለዋል፤ ኃጢአት ኃጢአተኛን ይጎዳል። 5በክፉ ነገር የሚደሰት ይኰነናል፤ 6ወሬን የሚጠላ ክፉን ያርቃል፤ 7የተነገረህን ፈጽሞ አትድገም፤ ከአደጋም ትጠበቃለህ። 8ለወዳጅም ሆነ ለጠላት ስላደረግኸው አትንገር፤ አለመንገርህ ኃጢአት ካልሆነ በቀር አትግለጸው። 9ብትናገር ይሰማብሃል፥ እንዲያ ከሆነ ደግሞ መታመንን ታጣለህ፤ ከጊዜም ብዛት ጥላቻን ታተርፋለህ። 10አንድ ምሥጢር ሰምተሃልን? ከአንተው ጋር ይቀበር፤ ድፍረት ይኑርህ፥ አያፈነዳህም። 11ሞኝ ሰው ስለ ሰማት ወሬ ይጨነቃል፤ በወሊድ ላይ እንዳለች ሴትም ያምጣል። 12በሞኝ ዘንድ የታወቀ ወሬ፥ በጭን ላይ እንደተሰካ ፍላጻ ነው።
የሰማኸውን ሁሉ አትመን
13ወዳጅህን ጠይቀው፥ ምናልባት ምንም አላደረገም ይሆናል፤ ካደረገም ዳግመኛ አያደርገውም። 14ባልንጀራህን ጠይቀው፥ ምናልባት ያለው ነገር አይኖርም ይሆናል፤ ተናግሮም ከሆነ አይደግመውም። 15ወዳድህን ጠይቀው፥ ሐሜት የተለመደ ነውና የሰማኸውን ሁሉ አትመን። 16አንዳንድ ሰው ክፉ ነገር ሳያስብ ያዳልጠዋል፤ ከቶስ በንግግሩ ያልበደለ ይኖራልን? 17ከማስፈራራትህ በፊት ባልንጀራህን ጠይቅ፤ የልዑል እግዚአብሔርን ሕግ ታዘዝ።#19፥17 18-19 እግዚአብሔርን መፍራት የርኅራኄውና ጥበቡን የመቀበል ውጤት መጀመርያ ነው። የጌታ ትእዛዛት እውቀት እና ሕይወት ሰጪ ሥርዓት ነው፤ የሚያስደስተውን እንዲፈጽሙ የሚያስችላቸው የሕያውነት ዛፍ ፍሬ ይለቅማሉና።
ትክክለኛና የተሳሳተ ጥበብ
20ጥበብ ማለት ጌታን መፍራት ነው፤ መሠረቱም ሕጉን መፈጸም ነው።#19፥20 21. ጌታውን፥ “አንት የምታዘኝን አልፈጽምም የሚል አገልጋይ የጌታውን ትእዛዝ ዘግይቶ እንኳ ቢፈጽም አሳዳሪውን ከማስቀየም አያመልጥም።” 22በክፋት መካን ግን ጥበብ አይደለም፤ የኃጢአተኞች ምክር ጥንቃቄ የጎደለው ነው። 23ጣዕም ያጣ ብልጥነት አለበት፥ ጥበብ የሌለው ሁሉ ሞኝ ነው። 24በብልጥነት ሕጉን ከመጣስ፥ በፍርሃት ለእርሱ አድሮ አላዋቂ መሆን ይቀላል። 25እንከን የማይወጣለት፥ ነገር ግን ታማኝነት የጐደለው ኃጢአት አለ። በሌሎች የዋህነት በመጠቀምም የሚያተርፉ አሉ። 26ኀዘን እንደከበደው ሁሉ ጐብጦ የሚሄድ ሰው አለ፥ በውስጡ ግን ከማታለል በቀር ምንም የለም። 27ፊቱን ይሸሽጋል፤ ያልሰማም ይመስላል፤ ካልተጋለጠ በቀር ባንተ ላይ ይሠራብሀል። 28ኃይል በማጣቱም ብቻ ከመበደል የሚታቀብ አለ፤ አጋጣሚውን ካገኘ ግን ወደ ኋላ አይልም። 29ሰውን በመልኩ መለየት ይቻላል፤ ተመራማሪ ደግሞ በፊቱ ገጽታ ይታወቀል። 30ሰው በአለባበሱ፥ በአሳሳቁ፥ በአነጋገሩ ይለያል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 19: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ