ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል፥ ነፍሴ መከራን ጠግባለችና፥ ሕይወቴም ወደ ሲኦል ቀርባለችና። ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥ ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ። ለዘለዓለም እንደማታስባቸው፥ እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ በሙታን ውስጥ እንዳሉ የተጣልሁ ሆንሁ፥ እነርሱም ከእጅህ ተለዩ። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ፥ በታችኛው ጉድጓድ አስቀመጥኸኝ። በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።
መዝሙረ ዳዊት 88 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 88:3-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች