በማይመለከተው ገብቶ የሚሟገት፥ ውሻን በጆሮው እንደሚይዝ ነው። ትንታግንና ፍላጻን ሞትንም እንደሚወረውር እንደ ዕብድ ሰው፥ ባልንጀራውን የሚያታልል፦ “ስቀልድ ነው” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው። እንጨት ባለቀ ጊዜ እሳት ይጠፋል፥ ጆሮ ጠቢ በሌለበትም ዘንድ ጠብ ጸጥ ይላል። ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንዲያበዛ፥ እንዲሁ ቁጡ ሰው ጠብን ያበዛል። የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥ እርሱም እስከ ሆድ ጉርጆች ድረስ ይወርዳል። ክፋት በልቡ ሳለ ፍቅርን የሚናገር ከንፈር በብር ዝገት እንደተለበጠ የሸክላ ዕቃ ነው።
መጽሐፈ ምሳሌ 26 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ምሳሌ 26:17-23
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች