እርሱ የእግዚአብሔር ባሕርይ ኖሮት ሳለ እንኳ ከእግዚአብሔር ጋር እኩልነትን እንደመንጠቅ አድርጎ አልቈጠረውም፤ ነገር ግን እንደ ሰው ሆኖ በመወለድ የባርያን መልክ ይዞ ራሱን ባዶ አደረገ፤ በሰው አምሳል ተገኝቶ፥ በትሕትና ራሱን ዝቅ አደረገ፤ በዚህም የመስቀልን ሞት እንኳ በመቀበል እስከ ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:6-8
3 ቀናት
የአስቴር መጽሐፍ የእግዚአብሔር ህዝብ ከዘር ወይም ከጅምላ ጥፋት ራሱን ሊከላከል እንኳን አቅም እንደሌለው በግልፅ ያሳያል፡፡ ራሷን አደጋ ውስጥ ጥላ ስለ ህዝቡ በንጉሱ ፊት ለመቆም ከህዝቡ ጋር በመሆን ራሷን ለየች:: ይህ የሶስት ቀናት የንባብ ዕቅድ የአስቴርን የጥንካሬና ፍቅር ታሪክ የሚዳስስና የክርስቶስን ታሪክ የሚያንፀባርቅ ሲሆን ይኸውም እርሱ እንደ እኛ ተቆጠሮ፣ ስለ እኛ መካከለኛ ሆኖ እና እኛ ራሳችንን ማዳን በማንችልበት ሁኔታ አዳነን፡፡
እግዚአብሔር የገባልህን የተስፋ ቃል እንዴት እንደሚፈፅመው ትገረም ይሆን? ፍሬያማ ኑሮስ ለመኖር ተስፋ ታደርጋለህ? የዕዝራ መጽሐፍ የሚዳስሰው እግዚአብሔር ህዝቡን ለመታደግና ለማደስ የተስፋ ቃሉን መፈፀሙን ሲሆን ከዚህም የተነሳ የኖሩትን ፍሬያማ ኑሮ ያሳያል፡፡ በዕዝራ አስደማሚ ታሪክ ውስጥ የሚታየው አግዚአብሔር ለሰው ዘር ሁሉ የገባው ትልቁ የተስፋ ፍፃሜ የሆነውና ብቸኛው የፍሬያማነት መንገድ የሆነው ኢየሱስ ነው፡፡
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች