የማቴዎስ ወንጌል 6:6-13

የማቴዎስ ወንጌል 6:6-13 መቅካእኤ

አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ በርህንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህ ይከፍልሃል። “ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ የሚደጋገሙ ቃላትን አትጠቀሙ፥ እነርሱ ብዙ በመናገራቸው የሚሰሙ ይመስላቸዋልና። ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሳትጠይቁት ያውቃልና። ስለዚህ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’

ተዛማጅ ቪዲዮዎች