አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፥ የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር። መልክተኛም ወደ ኢዮብ መጣ፤ እንዲህም ኣለው፦ “በሬዎች እያረሱ፥ በአጠገባቸውም አህዮች ተሰማርተው ሳሉ፥ የሳባ ሰዎች አደጋ ጣሉና ወሰዱአቸው፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው። እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀች፥ በጎቹንም አቃጠለች፥ ጠባቂዎችንም በላች፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው። እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ፦ “ከለዳውያን በሦስት ረድፍ ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው። እርሱም ገና ሲናገር ሌላ መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር፥ እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።” ኢዮብም ተነሣ መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ ተደፍቶ ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦ “ራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፥ ጌታ ሰጠ፥ ጌታ ወሰደ፥ የጌታ ስም የተባረከ ይሁን።”
መጽሐፈ ኢዮብ 1 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢዮብ 1:13-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች