መጽሐፈ መሳፍንት 7:13-16

መጽሐፈ መሳፍንት 7:13-16 መቅካእኤ

አንድ ሰው ያየውን ሕልም ለጓደኛው በሚነግርበት ጊዜ ጌዴዎን እዚያ ደረሰ። ያም ሰው፥ “በሕልሜ ክብ የሆነ አንድ የገብስ ቂጣ ከላይ ተንከባሎ በምድያማውያን ሰፈር ላይ ሲወርድ፥ ድንኳኑንም ሲመታው ከአመታተም ኀይለኛነት የተነሣድንኳኑ ተገልብጦ ሲፈራርስ አየሁ” በማለት ይነግረው ነበር። ጓደኛውም መልሶ፥ “ይህ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድያማውያንንና ሰፈሩን በሙሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶታልና” አለው። ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍቺውን በሰማ ጊዜ ለጌታ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፥ “ጌታ የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ!” አላቸው። ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፥ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።