መሳፍንት 7:13-16

መሳፍንት 7:13-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጌዴ​ዎ​ንም በደ​ረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕል​ምን ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ሲያ​ጫ​ውት፥ “እነሆ፥ ሕልም አለ​ምሁ፤ እነ​ሆም፥ አን​ዲት የገ​ብስ እን​ጎቻ ወደ ምድ​ያም ሰፈር ተን​ከ​ባ​ልላ ወረ​ደች፤ ወደ ድን​ኳ​ኑም ደርሳ እስ​ኪ​ወ​ድቅ ድረስ መታ​ችው፤ ገለ​በ​ጠ​ች​ውም፤ ድን​ኳ​ኑም ወደቀ” ይል ነበር። ባል​ን​ጀ​ራ​ውም መልሶ፥ “ይህ ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰው ከኢ​ዮ​አስ ልጅ ከጌ​ዴ​ዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ያ​ም​ንና ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ በእጁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አል” አለው። ጌዴ​ዎ​ንም ሕል​ሙ​ንና ትር​ጓ​ሜ​ዉን በሰማ ጊዜ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሰፈር ተመ​ልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን ሠራ​ዊት በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና ተነሡ” አለ። ሦስ​ቱ​ንም መቶ ሰዎች በሦ​ስት ወገን ከፈ​ላ​ቸው፤ በሁ​ሉም እጅ ቀንደ መለ​ከ​ትና ባዶ ማሰሮ፥ በማ​ሰ​ሮ​ዉም ውስጥ ችቦ ሰጣ​ቸው።