ትንቢተ ዕንባቆም መግቢያ
መግቢያ
ነቢዩ ዕንባቆም ከሌሎች ነብያት በተለየ መልኩ የአምላክን መንግሥት ፍትሕ በጥያቄ ያነሣል። መጽሐፈ ኢዮብ ውስጥም የጻድቅን ሰው መሰቃየት አስመልክቶ ጥያቄ ሲነሣ እንደሚታየው ዓይነት ነው። ዕንባቆም ተግዳሮት ሆኖበት በጥያቄ የሚያነሣው ጉዳይ ግን በነቢዩና በእግዚአብሔር መካከል በተደረገው ውይይት የታቀፈ ነው፤ በአንድ በኩል በአይሁድ ኅብረተሰብ ውስጥ ስለ ተንሰራፋው ኢፍትሐዊነት ቅሬታውን ያቀርባል (1፥2-4)፤ በሌላ በኩል (1፥5-11) ከለዳውያን፥ ማለትም ባቢሎናውያን በወረራ ለፈጸሙት በደል እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው ያሳስባል። ዕንባቆም የከለዳውያንን ጭካኔ አጥብቆ ያወግዛል (1፥12—2፥1)። ይህንንም የምንረዳው እግዚአብሔር መለኮታዊ ምላሹን ሲሰጥ ሰዎች በእርሱ መልካምና ታማኝ አስተዳደር ላይ መደገፍ እንደሚችሉ እያረጋገጠ ነው (2፥2-4)።
ይህ በዕንባቆም እና በእግዚአብሔር መካከል የተደረገው ንግግር በጨቋኝ አስተዳደር ውስጥ በተከታታይነት የሚከሠተውን አሰቃቂ ሁኔታ ያሳያል (2፥5-20)። እንዲሁም ምዕራፍ ሦስት አምላክ ቀደም ብሎ የተናገራቸውን ተስፋዎች ለመፈጸምና ሕዝቡን ለማዳን እንደሚመጣ ያብራራል።
ሁለት ዐበይት ክሥተቶች በዕንባቆም ትንቢት ውስጥ ይገኛሉ። አንደኛው ታላቂቷ ባቢሎን (605 ከክርስቶስ ልደት በፊት) በግብጻዊያን ላይ የተቀዳጀችው ድል ሲሆን፤ ሁለተኛው በኢየሩሳሌም ውድመት የተጠናቀቀው ባቢሎናውያን በአይሁድ ላይ ያካሄዱት ወረራ (587 ከክርስቶስ ልደት በፊት) ነው። በእነዚያ ዓመታት በይሁዳ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የነበረው አስከፊ ሁኔታ ስለ መለኮታዊ ፍትሕ ከሚነሡ አስቸጋሪ መለኮታዊ ጥያቄዎች ጋር ዕንባቆምን አፋጦታል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የዕንባቆም የመጀመሪያ ቅሬታ (1፥1-4)
የእግዚአብሔር ምላሽ (1፥5-11)
የዕንባቆም ሁለተኛ ቅሬታ (1፥12—2፥1)
የእግዚአብሔር ምላሽ (2፥2-4)
ክፉ ሰዎችን የሚቃወም ቃል (2፥5-20)
ስለ አምላክ ግዛት የሚገልጽ ቃል (3፥1-19)
ምዕራፍ
Currently Selected:
ትንቢተ ዕንባቆም መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ