2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:8-10

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:8-10 መቅካእኤ

ይህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ። እርሱ ግን፥ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ በድካም ፍጹም ይሆናል” አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል እንዲያድርብኝ በበለጠ ደስታ በድካሜ መመካትን እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፥ በመንገላታት፥ በችግር፥ በስደት፥ በጭንቀት፥ ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያንጊዜ እበረታለሁ።