2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ሁለተኛ ሲጀምር ንጉሥ ሰሎሞን የፈጸማቸውን ተግባራት በሰፊው በመዳሰስ ነው። ንጉሡ ሕዝቡን ለማስተዳደር ጥበብ ስለ መጠየቁንና ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ስለ መዘጋጀቱን ይገልጻል። እንዲሁም ንግሥት ሳባ እርሱንም መቅደሱን መጐብኘትዋን ይናገራል። በመቀጠልም በንጉሥ ሮብዓም ስሕተት ምክንያት ስለተከፋፈሉት ሁለት መንግሥታት ይተርካል። በተጨማሪም፥ በሃይማኖት ረገድ መታደስን ስላመጡት የይሁዳ ነገሥታት ይናገራል። ለምሳሌ ንጉሥ አሳ ከርኵሰት ምድሪቱን ስለማንጻቱ፥ ንጉሥ ሕስቅያስ ቤተ መቅደሱን ስለ ማንጻቱና የፋሲካን በዓል በድምቀት ስለማክበሩ፥ ንጉሥ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን ስለማደሱና የሕጉን መጽሐፍ በማግኘት የአምልኮ ሥርዓት ተሐድሶ ስለማምጣቱ ይገልጻል። በመጨረሻም የመጽሐፉ ሐሳብ የሚያበቃው የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በባቢሎን ላሉት አይሁዳውያን ወደ አገራቸው ተመልሰው ቤተ መቅደሱን እንዲሠሩ መፍቀዱን በመግለጽ ነው።
ዜና መዋዕል ሁለተኛ በሁለት ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል። አንደኛው ከምዕራፍ አንድ እስከ ዘጠኝ ያለው ሲሆን ንጉሥ ሰሎሞን ስላከናወናቸው ተግባራት ይገልጻል። ሁለተኛው ከምዕራፍ ዐሥር እስከ ሠላሳ ስድስት ያለው ሲሆን ለሁለት ስለተከፈለው የእስራኤል መንግሥት ያወሳል።
የመጽሐፉ አወቃቀር
1. የሰሎሞን ታሪክ (1፥1—9፥31)
1.1 ሰሎሞን፥ ጥበብ እና ሀብት (1፥1-17)
1.2 ሰሎሞን ለቤተ-መቅደሱ ሥራ ያደረገው ዝግጅት እና ግንባታ (2፥1—5፥1)
1.3 ሰሎሞን ቤተ መቅደሱን ለእግዚአብሔር ቀደሰው (5፥2—7፥22)
1.4 ሰሎሞን ዝና (8፥1—9፥31)
2. ስለተከፈለው የእስራኤል መንግሥት (10፥1—36፥23)
2.1 የእስራኤላውያን ከይሁዳ መለየት (10፥1-19)
2.2 የይሁዳ ነገሥታት (11፥1—28፥27)
2.3 የሕዝቅያስ ተሐድሶ እና የዘመነ መንግሥቱ ፍጻሜ (29፥1—32፥33)
2.4 ምናሴ እና አሞጽ (አሞን) (33)
2.5 የኢዮስያስ መታደስ (34፥1—35፥27)
2.6 የይሁዳ መውደቅ (36፥1-21)
2.7 የነፃነት አዋጅ (36፥22-23)
ምዕራፍ
Currently Selected:
2ኛ መጽሐፈ ዜና መዋዕል መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ