ወደ ሮም ሰዎች 14:1-3

ወደ ሮም ሰዎች 14:1-3 አማ05

በእናንተ መካከል በእምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው ተቀበሉት እንጂ በግል ሐሳቡ ላይ ክርክር አታንሡ። ለምሳሌ አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ለመብላት የሚያስችል እምነት ይኖረዋል፤ በእምነቱ ያልጸናው ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል፤ ስለዚህ ማንኛውንም ነገር የሚበላ ሰው የማይበላውን ሰው አይንቀፈው፤ የማይበላውም በሚበላው ሰው ላይ አይፍረድ፤ እርሱንም እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።