ወደ ሮም ሰዎች 11:26-29

ወደ ሮም ሰዎች 11:26-29 አማ05

እንግዲህ በዚህ ዐይነት እስራኤላውያን ሁሉ ይድናሉ። ስለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “አዳኝ ከጽዮን ይመጣል፤ ከያዕቆብም ዘር ሁሉ ክፋትን ያስወግዳል፤ ኃጢአታቸውንም በደመሰስኩላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው።” እስራኤላውያን የወንጌልን ቃል ባለመቀበላቸው ስለ እናንተ ስለ አሕዛብ ጥቅም የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነዋል፤ ነገር ግን በምርጫ በኩል በነገድ አባቶች ምክንያት የእግዚአብሔር ወዳጆች ናቸው። እግዚአብሔር ከመረጠና ጸጋውን ከሰጠ በኋላ ባደረገው ነገር ሐሳቡን አይለውጥም።