መጽሐፈ መዝሙር 42:1-3

መጽሐፈ መዝሙር 42:1-3 አማ05

አምላክ ሆይ! ዋላ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ። ሕያው አምላክ ሆይ! ውሃ የመጠማትን ያኽል አንተን እናፍቃለሁ፤ ፊትህን ለማየት ወደ አንተ የምመጣው መቼ ነው? ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።