መጽሐፈ መዝሙር 29:3-9
መጽሐፈ መዝሙር 29:3-9 አማ05
የእግዚአብሔር ድምፅ በውቅያኖሶች ላይ ያስተጋባል፤ የክብር አምላክ እግዚአብሔር ከሚናወጠው ማዕበል በላይ ያንጐደጒዳል። የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ ድምፁም ባለ ግርማ ነው። የእግዚአብሔር ድምፅ የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዛፍ ይሰብራል። የሊባኖስን ተራራዎች እንደ እንቦሳ እንዲፈነጩ ያደርጋቸዋል፤ የስርዮንንም ተራራ እንደ ጐሽ ጥጃ እንዲዘል ያደርገዋል። የእግዚአብሔር ድምፅ መብረቅን ብልጭ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ድምፅ በረሓን ያናውጣል፤ የቃዴስንም በረሓ ያንቀጠቅጣል፤ የእግዚአብሔር ድምፅ አጋዘንን እንድትወልድ ያደርጋል የዛፎችን ቅጠል ያረግፋል፤ በመቅደሱም ያሉ ድምፁን ሲሰሙ “ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን!” ይላሉ።

