መዝሙር 29:3-9

መዝሙር 29:3-9 NASV

የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ። የእግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው። የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል። ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣ ሢርዮንንም እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል። የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል። የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤ የእግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል። የእግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤ ጫካዎችንም ይመነጥራል፤ ሁሉም በርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።