ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:14-20

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:14-20 አማ05

ይሁን እንጂ እናንተ የችግሬ ተካፋዮች ሆናችሁ በመገኘታችሁ መልካም አደረጋችሁ። ከዚህም በቀር ወንጌልን ለማብሠር በጀመርኩበት ጊዜ ከመቄዶንያ ስወጣ ከእናንተ በፊልጵስዩስ ከምትገኙት አማኞች በቀር በመስጠትም ሆነ በመቀበል ከእኔ ጋር የተባበረ ሌላ ማኅበረ ምእመናን እንዳልነበረ እናንተው ራሳችሁ ታውቃላችሁ። በተሰሎንቄም ችግር እንደ ደረሰብኝ ዐውቃችሁ መላልሳችሁ ርዳታ ልካችሁልኛል። ይህንንም ስል የእናንተን ስጦታ ለማግኘት በመጓጓት ሳይሆን የልግሥናችሁ ፍሬ እንዲበዛላችሁ በመመኘት ነው። የሚያስፈልገኝንና ከሚያስፈልገኝም በላይ የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ፤ ይህም የእናንተ ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአብሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው። ስለዚህም አምላኬ ከክብሩ ብልጽግና በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል። ለአባታችንና ለአምላካችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።