የሉቃስ ወንጌል 7:37-38

የሉቃስ ወንጌል 7:37-38 አማ05

በዚያች ከተማ አንዲት ኃጢአተኛ ሴት ነበረች፤ እርስዋም ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት ምሳ መጋበዙን በሰማች ጊዜ ሽቶ የሞላበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች። ከኢየሱስ በስተኋላ በእግሮቹ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች እግሮቹን በእንባዋ ታርስና በጠጒርዋ ታብስ ነበር፤ እግሮቹን እየሳመች ሽቶ ትቀባቸው ነበር።