መጽሐፈ ኢያሱ 22:1-5

መጽሐፈ ኢያሱ 22:1-5 አማ05

ከዚህ በኋላ ኢያሱ የሮቤልን፥ የጋድንና በምሥራቅ ያሉትን የምናሴን ነገዶች በአንድነት ጠርቶ፥ እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንድታደርጉት ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽማችኋል፤ የእኔንም ትእዛዝ ሁሉ ጠብቃችኋል፤ በዚህ ጊዜ ሁሉ ወገኖቻችሁን እስራኤላውያንን የከዳችሁበት ጊዜ የለም፤ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽማችኋል። እነሆ አሁን አምላካችሁ እግዚአብሔር በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ሰላምን ሰጥቶአቸዋል፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ወደ ሰጣችሁ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምሥራቅ ወደሚገኘውና ርስት አድርጋችሁ ወደ ወረሳችሁት ምድር ተመልሳችሁ ሂዱ፤ ሙሴ የሰጣችሁን ሕግና ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ውደዱ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ ትእዛዙንም ጠብቁ፤ ለእርሱም ታማኞች ሆናችሁ በሙሉ ልባችሁ፥ በፍጹም ሐሳባችሁ አገልግሉት።”