መጽሐፈ ኢያሱ 1:1-6

መጽሐፈ ኢያሱ 1:1-6 አማ05

የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ከሞተ በኋላ፥ የሙሴ ረዳት የነበረውን የነዌን ልጅ ኢያሱን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል አነጋገረው፤ “እነሆ! አገልጋዬ ሙሴ ሞቶአል፤ እንግዲህ አንተና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እኔ ለእናንተ ለእስራኤል ልጆች ወደማወርሳት ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ለመሻገር ተዘጋጁ። ለሙሴ ቃል በገባሁለት መሠረት በእግራችሁ የምትረግጡትን ምድር ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ። ድንበራችሁ በስተደቡብ ካለው ምድረ በዳ ተነሥቶ በስተሰሜን እስከሚገኙት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች ድረስ፥ በስተምሥራቅ ከትልቁ ወንዝ ከኤፍራጥስ፥ በመነሣት የሒታውያንን ምድር ሁሉ ጨምሮ በምዕራብ በኩል እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሆናል። አንተ ኢያሱ፥ በምትኖርበት ዘመን ሁሉ አንተን ተቋቊሞ ድል የሚነሣህ ማንም አይኖርም፤ እኔ ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር እሆናለሁ፤ ሁልጊዜም ከአንተ ጋር ነኝ፤ ከቶም አልተውህም፤ አይዞህ፤ በርታ፤ እኔ ለቀድሞ አባቶቻቸው ልሰጣቸው ቃል የገባሁላቸውን ምድር ለማውረስ ለእነዚህ ሕዝብ መሪ ትሆናለህ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}