ቶማስ “ጌታ ሆይ! ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፤ ታዲያ፥ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “መንገድና እውነት ሕይወትም እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ማንም ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔን ዐውቃችሁኝ ቢሆን ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ታውቁታላችሁ፤ አይታችሁታልም።” ፊልጶስም “ጌታ ሆይ! አብን አሳየንና ይበቃናል” አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ፊልጶስ ሆይ! ይህን ያኽል ጊዜ ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ ታዲያ፥ አንተ ‘አብን አሳየን’ እንዴት ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? ለእናንተ የምናገረውን ቃል የምናገረው በራሴ ሥልጣን አይደለም፤ ነገር ግን ሥራውን ሁሉ የሚሠራው፥ በእኔ የሚኖረው አብ ነው። እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ እመኑ፤ አለበለዚያ በሥራዎቼ ምክንያት እመኑኝ። እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ ይሠራል፤ እንዲያውም ከዚህ የበለጠ ይሠራል፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁ። አብ በወልድ ምክንያት እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርግላችኋለሁ። ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።”
የዮሐንስ ወንጌል 14 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 14:5-14
5 ቀናት
IN ENGLISH): ይህ የ5 ቀናት የንባብ ዕቅድ ኢየሱስን ለመመስከር በዕውቀትና በድፍረት ያስታጥቅሃል፡፡ በጨለማው ላይ ብርሃን ሁን፡፡
9 ቀናት
ጌታ ኢየሱስ ስለ አገልግሎቱ ሲናገር ዓላማው ለሰዎች የዘላለም ሕይወት መስጠት እንደሆነ ተናግሯል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” (ዮሐ. 3፡16)። ይህ የዘላለም ሕይወት ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ የዘላለም ሕይወት ምን እንደሚል እንመልከት።
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች