ጌዴዎን እዚያ በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ያየውን ሕልም ለጓደኛው ሲነግረው ሰማ፤ ሕልሙም እንዲህ የሚል ነበር፦ “አንዲት የገብስ ቂጣ ከላይ ተንከባልላ ወርዳ ወደ ምድያም ሰፈር ደርሳ በዚያ ያለውን ድንኳን መታችው፤ ድንኳኑም ተገልብጦ በምድር ላይ ተዘረጋ።” ጓደኛውም “ይህማ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ ነው! ከቶ ሌላ ትርጒም ሊሰጠው አይችልም፤ እግዚአብሔር ለጌዴዎን በምድያምና በመላው ሠራዊታችን ላይ ድልን ሰጥቶታል!” ሲል መለሰለት። ጌዴዎን ስለ ሰውየው ሕልምና ስለ ፍቹም ምንነት በሰማ ጊዜ በጒልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤላውያንም ሰፈር ተመልሶ “እግዚአብሔር በምድያማውያንና በሠራዊቱ ላይ ድልን የሚያቀዳጃችሁ ስለ ሆነ ተነሡ!” አላቸው። ሦስት መቶዎቹንም ሰዎች ከፍሎ በሦስት ቡድን መደባቸው፤ ለእያንዳንዱም ሰው አንድ እምቢልታና በውስጡ ችቦ ያለበት አንድ ማሰሮ ሰጠ።
መጽሐፈ መሳፍንት 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መሳፍንት 7:13-16
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች