ተጨነቁ፤ እዘኑ፤ አልቅሱ፤ ሳቃችሁ ወደ ለቅሶ፥ ደስታችሁ ወደ ሐዘን ይለወጥ። በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል። ወንድሞች ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ፤ ሰውን የሚያማ ወይም በሰው ላይ የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ላይ ይፈርዳል፤ በሕግ ላይ ብትፈርድ ደግሞ ፈራጅ መሆንህ ነው እንጂ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም። ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ሊያድንም ሊያጠፋም የሚችል እርሱ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ በሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እናንተ “ዛሬ ወይም ነገ ወደ እንዲህ ያለ ከተማ ሄደን እዚያ አንድ ዓመት እንቀመጣለን፤ ነግደንም እናተርፋለን” የምትሉ ተጠንቀቁ። ነገ የሚሆነውን አታውቁም፤ ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ለአንድ አፍታ ታይቶ በኋላ እንደሚጠፋ ጉም ናችሁ። ይልቁንስ እናንተ ማለት የሚገባችሁ “ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ይህን ወይም ያን እናደርጋለን” ነው። እናንተ ግን ይህን በማለት ፈንታ በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲህ ያለው ትምክሕት ሁሉ ክፉ ነው። እንግዲህ መልካም ነገር ማድረግን እያወቀ የማያደርግ ሰው አለማድረጉ ኃጢአት ይሆንበታል።
የያዕቆብ መልእክት 4 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የያዕቆብ መልእክት 4:9-17
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች