የያዕቆብ መልእክት 1:2-5

የያዕቆብ መልእክት 1:2-5 አማ05

ወንድሞቼ ሆይ! ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ ደስ የሚያሰኙ ነገሮችን እንዳገኛችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ። የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥት የሚያስገኝላችሁ መሆኑን ታውቃላችሁ። በትዕግሥት መጽናታችሁ ምንም ሳይጐድልባችሁ ፍጹምና ሙሉ እንድትሆኑ የሚያበቃችሁ ይሁን። ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።