ወደ ገላትያ ሰዎች 4:28-31

ወደ ገላትያ ሰዎች 4:28-31 አማ05

ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተም እንደ ይስሐቅ የተስፋው ቃል ልጆች ናችሁ። ነገር ግን በዚያን ጊዜ በሥጋ የተወለደው በመንፈስ የተወለደውን እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው። ነገር ግን ቅዱስ መጽሐፍ የሚለው ምንድን ነው? ቅዱስ መጽሐፍ “አገልጋይቱ ሴት የወለደችው ልጅ ነጻይቱ ሴት ከወለደችው ልጅ ጋር አብሮ ስለማይወርስ አገልጋይቱን ከነልጅዋ ወዲያ አስወጣት” ይላል። ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፥ እኛ የነፃይቱ ልጆች ነን እንጂ የአገልጋይቱ ልጆች አይደለንም።