ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:3-4

ትንቢተ ሕዝቅኤል 34:3-4 አማ05

ወተቱን ትጠጣላችሁ፤ ከጠጒራቸው የተሠራውንም ሱፍ ትለብሳላችሁ፤ የሰባውንም በግ ዐርዳችሁ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን በጎችን በማሰማራት አትጠብቁም፤ የደከሙትን አላበረታቸሁም፤ የታመሙትን አላዳናችሁም፤ የተሰበሩትን አልጠገናችሁም፤ የባዘኑትን አልመለሳችሁም፤ የጠፉትን አልፈለጋችሁም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በግፍና በጭካኔ ገዛችኋቸው።