ኦሪት ዘዳግም 11:22-25
ኦሪት ዘዳግም 11:22-25 አማ05
“ስለዚህም እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውደዱ፤ በእርሱ መንገድም በመጓዝ ለእርሱ ታማኞች ሁኑ። ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር እነዚህን በፊታችሁ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያስወጣል፤ እናንተም በብዛትና በኀይል ከእናንተ እጅግ ብርቱዎች የሆኑትን ሕዝቦች ምድር ትወርሳላችሁ። ስታልፉ በእግራችሁ የምትረግጡት መሬት ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም በደቡብ በኩል ካለው በረሓ ተነሥቶ በሰሜን በኩል እስካሉት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች፥ እንዲሁም በምሥራቅ በኩል ከሚገኘው ከኤፍራጥስ ወንዝ ተነሥቶ በምዕራብ በኩል እስከሚገኘው እስከ ታላቁ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሰፋል። በዚያች ምድር በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ሕዝቦች ሁሉ እንዲፈሩአችሁ ያደርጋል፤ ሊቋቋማችሁ የሚችልም ከቶ አይገኝም።

