የሐዋርያት ሥራ 9:26-28

የሐዋርያት ሥራ 9:26-28 አማ05

ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም በሄደ ጊዜ እዚያ ካሉት ደቀ መዛሙርት ጋር ለመደባለቅ ሞከረ፤ እነርሱ ግን የእርሱ በክርስቶስ ማመን እውነት ስላልመሰላቸው ሁሉም ፈሩት። በርናባስ ግን ሳውልን ወደ ሐዋርያት አቀረበውና በመንገድ ሳለ ጌታ እንዴት እንደ ተገለጠለትና እንዳነጋገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም እንዴት በድፍረት እንዳስተማረ ነገራቸው። ስለዚህ ሳውል ከእነርሱ ጋር ሆኖ በኢየሩሳሌም ይዘዋወር ነበር። በጌታም ስም በድፍረት ያስተምር ነበር፤