የሐዋርያት ሥራ 4:8-13

የሐዋርያት ሥራ 4:8-13 አማ05

በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ! እኛ ዛሬ የምንጠየቀው ለአንድ ሽባ ሰው ስለ ተደረገለት መልካም ሥራና በምን ዐይነት ሁኔታ እንደ ዳነ ነው። ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን። እናንተ ግንበኞች ንቃችሁ የጣላችሁትም ድንጋይ እርሱ ነው፤ ነገር ግን እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ። ስለዚህ መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም።” ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረት መናገራቸውን የሸንጎ አባሎች ባዩ ጊዜ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ያውቁ ስለ ነበረ ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ዐወቁ፤