ዘካርያስ 8:1-8

ዘካርያስ 8:1-8 NASV

እንደ ገናም የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ፤ ስለ እርሷም በቅናት ነድጃለሁ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌም እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ተራራም ቅዱስ ተራራ ይባላል።” የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሽማግሌዎችና አሮጊቶች እንደ ገና በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፤ እያንዳንዳቸውም ከዕድሜያቸው ብዛት የተነሣ ምርኵዝ ይይዛሉ። የከተማዪቱም አደባባዮች እዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።” እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ጊዜ ይህ ለቀረው የእስራኤል ሕዝብ አስደናቂ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ ለእኔ ግን አስደናቂ ሊሆን ይችላልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሕዝቤን ከምሥራቅና ከምዕራብ አገር እታደጋለሁ። በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በጽድቅና በታማኝነት አምላካቸው እሆናለሁ።”