ከመዝሙር ሁሉ የሚበልጥ የሰሎሞን መዝሙር። በከንፈሩ መሳም ይሳመኝ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ደስ ያሰኛልና። የሽቱህ መዐዛ ደስ ያሰኛል፤ ስምህ እንደሚፈስስ ሽቱ ነው፤ ታዲያ ቈነጃጅት ቢወድዱህ ምን ያስደንቃል! ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን! ንጉሡ ወደ ዕልፍኞቹ አምጥቶኛል። በአንተ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እንወድሳለን። አንተን እንደዚህ ማፍቀራቸው ትክክል ነው። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ እኔ ጥቍር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ ጥቍረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣ እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው። ጥቍር ስለ ሆንሁ ትኵር ብላችሁ አትዩኝ፤ መልኬን ያጠቈረው ፀሓይ ነውና፤ የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቈጡኝ፤ የወይን ተክል ቦታዎችም ጠባቂ አደረጉኝ፤ የራሴን የወይን ተክል ቦታ ተውሁት።
ማሕልየ መሓልይ 1 ያንብቡ
ያዳምጡ ማሕልየ መሓልይ 1
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማሕልየ መሓልይ 1:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች