ሮሜ 14:19-21

ሮሜ 14:19-21 NASV

ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችንም የምንተናነጽበትን ማንኛውንም ጥረት እናድርግ። ለምግብ ስትል የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ለሌላው ሰው የመሰናከያ ምክንያት የሚሆነውን መብላት ስሕተት ነው። ለወንድምህ መሰናከል ምክንያት የሚሆነውን ሥጋን አለመብላት፣ ወይንን አለመጠጣት፣ ወይም አንዳች ነገርን አለማድረግ መልካም ነው።