ራእይ 21:22-27

ራእይ 21:22-27 NASV

ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክና በጉ መቅደሷ ስለ ሆኑ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ቤተ መቅደስ አላየሁም። የእግዚአብሔር ክብር ብርሃን ስለሚሰጣትና በጉም መብራቷ ስለ ሆነ፣ ከተማዋ ፀሓይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጋትም። ሕዝቦች በብርሃኗ ይመላለሳሉ፤ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ። በዚያ ሌሊት ስለሌለ፣ በሮቿ በየትኛውም ቀን አይዘጉም። የሕዝቦች ግርማና ክብር ወደ እርሷ ይገባል። በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፣ ርኩሰትን የሚያደርግና ውሸትን የሚናገር ሁሉ አይገባባትም።