ራእይ 12:7-11

ራእይ 12:7-11 NASV

በሰማይም ጦርነት ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋራ ተዋጉ፤ ዘንዶውና መላእክቱም መልሰው ተዋጓቸው፤ ነገር ግን ድል ተመቱ፤ በሰማይም የነበራቸውን ስፍራ ዐጡ። ታላቁ ዘንዶ፣ የጥንቱ እባብ ተጣለ፤ እርሱም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው፣ ዓለምን ሁሉ የሚያስተው ነው፤ እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከርሱ ጋራ ተጣሉ። ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኀይልና መንግሥት፣ የርሱ ክርስቶስ ሥልጣንም መጥቷል። ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት ሲከስሳቸው የነበረው፣ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሏልና። እነርሱም በበጉ ደም፣ በምስክርነታቸውም ቃል፣ ድል ነሡት፤ እስከ ሞት ድረስ እንኳ፣ ለነፍሳቸው አልሳሱም።