መዝሙር 95:6-11

መዝሙር 95:6-11 NASV

ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤ በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤ እርሱ አምላካችን ነውና፤ እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣ የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን። ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣ በመሪባም እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ። ሥራዬን ቢያዩም፣ አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም። ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤ እኔም፣ “በልቡ የሳተ ሕዝብ ነው፤ መንገዴንም አላወቀም” አልሁ። ስለዚህ እንዲህ ብዬ በቍጣዬ ማልሁ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።”