እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም። ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ። ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣ ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣ ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ኀያል ነው። ምስክርነትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ ቤትህ በቅድስና ይዋባል።
መዝሙር 93 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 93
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 93:1-5
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች