መዝሙር 92:1-4

መዝሙር 92:1-4 NASV

እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፤ ልዑል ሆይ፤ ለስምህ መዘመር ጥሩ ነው፤ ምሕረትህን በማለዳ፣ ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤ ዐሥር አውታር ባለው በገና፣ በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ።