መዝሙር 90:10-16

መዝሙር 90:10-16 NASV

የዕድሜያችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጕዳለን። የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል? መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው። ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን። እግዚአብሔር ሆይ፤ ተመለስ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ለአገልጋዮችህም ራራላቸው። በዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለን፣ ሐሤትም እንድናደርግ፣ ምሕረትህን በማለዳ አጥግበን። መከራ ባሳየኸን ዘመን መጠን፣ ክፉም ባየንባቸው ዓመታት ልክ ደስ አሠኘን። ሥራህ ለአገልጋዮችህ፣ ክብርህም ለልጆቻቸው ይገለጥ።