መዝሙር 89:8-11

መዝሙር 89:8-11 NASV

የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል። የባሕርን ቍጣ ትቈጣጠራለህ፤ ሞገዱም ሲነሣ ጸጥ ታደርገዋለህ። አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤ በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው። ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤ ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አንተ መሠረትህ።