መዝሙር 69:10-13

መዝሙር 69:10-13 NASV

ነፍሴን በጾም ባስመረርሁ ጊዜ፣ እነርሱ ሰደቡኝ። ማቅ በለበስሁ ጊዜ፣ መተረቻ አደረጉኝ። በቅጥሩ ደጅ ለሚቀመጡት የመነጋገሪያ ርእስ፣ ለሰካራሞችም መዝፈኛ ሆንሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ግን በወደድኸው ሰዓት፣ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አምላክ ሆይ፤ በታላቅ ምሕረትህ፣ በማዳንህም ርግጠኛነት መልስልኝ።