መዝሙር 57:1-3

መዝሙር 57:1-3 NASV

ማረኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረኝ፤ ነፍሴ አንተን መጠጊያ አድርጋለችና፤ በክንፎችህ ሥር እጠለላለሁ። ለእኔ ያሰበውን ወደሚፈጽምልኝ አምላክ፣ ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ። ከሰማይ ልኮ ያድነኛል፤ የረገጡኝን ያዋርዳቸዋል፤ ሴላ እግዚአብሔር ምሕረቱንና ታማኝነቱን ይልካል።