መዝሙር 56:3-6

መዝሙር 56:3-6 NASV

ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ። ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል? ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ። ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።