እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል። ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ በላዬ ቆሙ፤ በትዕቢት የሚዋጉኝ ብዙዎች ናቸውና። ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ። ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል? ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ። ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፋታቸው የተነሣ እንዳያመልጡ፣ ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው። ሰቈቃዬን መዝግብ፤ እንባዬን በዕቃህ አጠራቅም፤ ሁሉስ በመዝገብህ የተያዘ አይደለምን? ወደ አንተ በተጣራሁ ቀን፣ ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ በዚህም፣ አምላክ ከጐኔ መቆሙን ዐውቃለሁ። ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣ ቃሉን በማመሰግነው በእግዚአብሔር፣ በአምላክ ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል? እግዚአብሔር ሆይ፤ የአንተ ስእለት አለብኝ፤ የማቀርብልህም የምስጋና መሥዋዕት ነው፤ በሕያዋን ብርሃን፣ በእግዚአብሔር ፊት እመላለስ ዘንድ፣ ነፍሴን ከሞት፣ እግሬንም ከመሰናክል አድነሃልና።
መዝሙር 56 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 56
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 56:1-13
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች