መዝሙር 50:9-12

መዝሙር 50:9-12 NASV

እኔ ግን ኰርማህን ከበረት፣ ፍየሎችህንም ከጕረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤ የዱር አራዊት ሁሉ፣ በሺሕ ተራሮች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና። በየተራራው ያለውን ወፍ ሁሉ ዐውቃለሁ፤ በሜዳ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ የእኔ ነው። ብራብ ለአንተ አልነግርህም፤ ዓለምና በውስጧ ያለውም ሁሉ የእኔ ነውና።