እግዚአብሔር ሆይ፤ በቍጣህ አትገሥጸኝ፤ በመዓትህም አትቅጣኝ። ፍላጻዎችህ ወግተውኛልና፤ እጅህም ተጭናኛለች። ከቍጣህ የተነሣ ሰውነቴ ጤና አጥቷል፤ ከኀጢአቴም የተነሣ ዐጥንቶቼ ሰላም የላቸውም። በደሌ ውጦኛል፤ እንደ ከባድ ሸክምም ተጭኖኛል። ከቂልነቴ የተነሣ፣ ቍስሌ ሸተተ፤ መገለም፤ ዐንገቴን ደፋሁ፤ ጐበጥሁም፤ ቀኑንም ሙሉ በትካዜ ተመላለስሁ። ወገቤ እንደ እሳት ነድዷል፤ ሰውነቴም ጤና የለውም። እጅግ ዝያለሁ፤ ፈጽሞም ደቅቄአለሁ፤ ከልቤም መታወክ የተነሣ እጮኻለሁ። ጌታ ሆይ፤ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ግልጽ ነው፤ ጭንቀቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም። ልቤ በኀይል ይመታል፤ ጕልበት ከድቶኛል፤ የዐይኔም ብርሃን ጠፍቷል።
መዝሙር 38 ያንብቡ
ያዳምጡ መዝሙር 38
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙር 38:1-10
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች