መዝሙር 30:6-10

መዝሙር 30:6-10 NASV

እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣ “ከቶ አልናወጥም” አልሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ ተራሮቼ ጸኑ፣ ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ ውስጤ ታወከ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤ “በእኔ ወደ ጕድጓድ መውረድ፣ በመሞቴ ምን ጥቅም ይገኛል? ዐፈር ያመሰግንሃልን? ታማኝነትህንስ ይናገራልን? እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”